በዓላት
በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚከበሩ በዐላት
ፋሲካ
‘ ወይቤሉን ፡ አትደንግፃ፡፡ ኢየሱስሃኑ፡ ናዝራዊ፡ተኀሥሡ፡ ዘተሰቅለ፡፡ ተንሥአ፡ ወኢሀሉ፡ ዝየስ፡ ወናሁ፡ መካኑ፡ ኀበ፡ ተቀብረ፡፡ ”
/እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፡ አትደንግጡ፡ የምትፈልጉት የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ነው፡ እርሱ ተነስቶአል፡ እዚህ የለም፡ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውላችሁ፡፡/ ማርቆስ 16፤6
ጌታችን ፣ መድኀኒታችን ና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሁላችን በደል እና ሐጢያት መከራን ተቀብሎ በመስቀል ላይ ከሞተ በሁዋላ ፡ በሶስተኛው ቀን ከሞት ተነስቶአል፡፡ ይህ ብርሃነ ትንሳኤው ነው በመላው ዓለም የፋሲካ በዐል ተብሎ የሚታወቀው ፡፡
ፋሲካ የስሙ ትርጉዋሜ ማለፍ ማለት ሲሆን፤ ይህም እስራኤላውያን ከ 430 በግብጽ በባርነት አገዛዝ ከነበሩበት አሰጨናቂ ዓመታት ነጻ የወጡበት ቀን ነው፡፡ በዚያም ቀን ምሽት በሁሉ ቤት ታርዶ የነበረው ጠቦት ፣ በበራቸው ጉበንና በመቃናቸው የለቀለቁት ደም ምሳሌነቱ ክርስቶስና የክርስቶስ ደም ነው፡፡ጌታችን እኛን ከሐጢያትና ከኩነኔ ሊያድነን ዋጋ ከፍሎአል፡፡ አሁን በአዲስ ኪዳን ዘመን ከ ዓለም ልንወጣ የምንችለው ደግሞ የአዲስ ኪዳኑን / የፋሲካውን በግ / በማመንና በመቀበል ሲሆን ፣ በቀራኒዮ በፈሰሰው ደሙም ከሚመጣው ቁጣ ማምለጥ እንችላለን፡፡ ደሙን በጉበኑ ባላደረገ ቤት ሁሉ ሞት እንደነበረ፡ በክርስቶስ ደም ያልነጻ እና የደሙ ማህተም በግንባሩ የሌለ ማንኛውም ሰው ከዘላለም ሞትና ፍርድ ማምለጥ አይችልም፡፡
እርሶም ዛሬ ከግብጽ / ከዓለም / ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በክርስቶስ አምልጠው አውነተኛውን የክርስትና ህይወት ሊኖሩ የሚወስኑበት ጊዜ እንዲሆን እመኝልዎታለሁ፡፡ በዛሬዋ ቀን በመስቀል ላይ ስለ እርሶ ሞቶ የተነሳውን ጌታ ና መድሓኒት በልብዎ ውስጥ ስፍራ ይስጡት፡፡ እስቲ የቀረዎትን ዘመን ለሞተውና ለተነሳው ጌታ ሊሰጡት ዛሬ ይወስኑ! እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይረዳዎታል፡
ኃጢአተኛ ከሆንክ በቅድስናው ደጅ ምን ትሠራለህ?
ብዙውን ጊዜ ወጣት ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ከብዙዎች ስሜት መረዳት እንደሚቻለው በኃጢአት ስንወድቅና በኛ ውስጥ ያለው ክርስቲያናዊ ማንነት ከሰዎች ሁሉ በተለየ መልኩ ቆሻሻ ሆኖና መስሎ ከታየን፤ ከቅድስት ቤተክርቲያን፤ ከጸጋው ግምጃ ቤት፤ ከምሕረቱ አደባባይ መራቅን እንደ መፍትሔ አድርገን እንወስዳለን፡፡ ምክንያቱስ ያልን እንደሆነ ጥንተ ጠላትዲያቢሎስ ሰዎችን የግሉ የሚያደርግበት ትልቁ ታክቲክ ቢኖር፤ አስቀድሞ ወደ ኃጢአትእንገባ ዘንድ ሁኔታዎችን ሁሉ በማመቻቸት፤ ስሜትን ከኅሊና በላይ አድርጎ በመሾም ማዘዝ፤አንተ/አንቺ ከማን ትለያለህ/ትለያለሽ፤ ይህን ኃጢአት እንኳን አንተ መምህራኑ፤ ቀዳሾቹ፤ ካህናቱ፤መዘምራኑ ሁሉ የሚሠሩት አይደለምን? የምን ማካበድ ነው በርታ በማለት ይገፋፋሀል፡፡ኃጢአትን ካሠራንና የሚፈልገውን ሁሉ ካስፈጸመ በኋላ ደግሞ ይህ ካንተ አይጠበቅም ነበር፡፡ሁሉ በንጽህና በቤቱ ሲኖሩ አንተ ግን ቆሽሸሐል፤ ረክሰሀል፤ ዋጋም የለሕም፤ ጥፋትህን ደግሞአምላክህም፤ ቅዱሳኑም፤ ጓደኞችህም ወዳጅ ጠላትህም አውቀውብሀል፡፡ ስለዚህ አትሞኝ ኃጢአተኛነህ ከደጁ ምን ትሠራለህ? አንተን ብሎ አስቀዳሽ፤ ቆራቢ፤አገልጋይ ስለዚህም ማንንም አታግኝ፤፤መንፈሳውያን ወንድሞችህን ወይም እህቶችህን በመንገድም ካየህ ሽሽ፡፡ ሰላምም አትበላቸውይልሀል፡፡ ይህ እውነት በእኔ ወይ በአንቺ ወይም በእናንተ ላይ የታየ መንፈሳዊ ፈተና ነው፡፡ ውሸትነው ብለን ልንሸሸው የማንችለው ሐቅ ነው፡፡ነገር ግን እናስተውል ይሁዳ አምላኩን አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት በርካታ የመዳን እድሎችንአሳልፏል፡፡ ለመታነቅ ሲነሳ ዛፏ ሸሽታዋለች፤ ንጹህ ደም አሳልፌ በመስጠቴ ተጸጽቻለሁ ሲልየነገረውን ውሳጣዊ ልቡናና መልእክት ገድሏል፡፡ ይልቁንም ጸጸቱን ሄዶ የተናገረው ለጸሐፍት እናፈሪሳውያን፤ለቀራጮች እና ለነፍሰ ገዳዮች ስለነበር እንዳልነው ባንተ አልተጀመረም አይነት ስብከትሲሰብኩት ነው ወደ መታነቁ ነው የሮጠው፡፡ ምናለ ለቅዱስ ጴጥሮስ፤ ለቅዱስ ዩሐንስ፤ለቅዱስያእቆብ እና ለሌሎቹ ወንድሞቹ ነግሮ ቢሆን? ተው ወንድሜ ንሰሐ ግባ ብለው የጴጥሮስን እንባባላበሱት ነበር፡፡እንደ ዘኪዎስም ጌታችን ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል እንዳለ፤ ለይሁዳም መዳንበሆነለት ነበር፡፡ስለዚህ ክርስቲያኖች፤ በሐጢአት ምክኒያት ከቅዳሴው፤ከማእጠንቱ፤ከደጀሰላሙ፤ከጉባኤው ሽሹ የሚል የጠላት መልእክት እና ጥሪ ሲመጣ ከእኔ ሽሽ፤የምኖረው እኮ ይቅርባይ እና ከባቴ አበሳ በሆነው አምላኬ ቤት ነው ልንል ይገባል፡፡ይህ ማለት ግን በመጽሐፈ ሲራክ የእግዚአብሔር ቸርነት ብዙ ነው እያልክ በሐጢአት ላይሐጢአትን አታድርግ ሲራክ 5፡-1 እንደተባለ በቸርነቱ ላይ መዘባበት እንዳያመጣ ጥንቃቄ ማድረግያስፈልጋል፡፡ቸርነቱ ለጽድቃችን ዋስትና እንጂ ሐጢአትን እየደጋገሙ እርሱ ይቅር ባይ ነውእንድንል አይደለምና በማስተዋል ልንጓዝ ይገባል፡፡ስለዚህም ጠላት ሰይጣን በሐጢአት ሰበብ ከቤቱ፤ከደጀ ሰላሙ፤ ከቅድስናው አውደ ምህረት ሊያርቀን እና የውስጥ ሰላሙ የተዛባ ብኩን ስብእናንሊያላብሰን በተነሳ ጊዜ፤ተው አንተ ሰይጣን ከእኔ ራቅ፤ሐጢአተኛም ብሆን አንድ ቀንያነጻኛል፤በቤቱም
ኃጢአተኛ ከሆንክ በቅድስናው ደጅ ምን ትሠራለህ?
ወርሀዊ፡

