በገቢ አመንጪ የምርትና አገልግሎት ዘርፍ በመሰማራት ቁሳዊ ሀብቶችን ማፍራትና ለመንፈሳዊ ተግባራት አጋዥ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በሥልጠናና በሙያ አገልግሎት ሥራዎች አባላቱን ተሳታፊ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት፡፡
የሰ/ት/ቤቱ ልማት ክፍል የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል
ሀ. የክፍሉን የሥራ እቅድና የበጀት ረቂቅን በማዘጋጀት ማጸደቅ፣ ተግባራዊ ማድረግ
ለ. ልማትን በተመለከተ የአሰራር ሥርአት መዘርጋት፣የአፈጻጸም መመሪያ ማዘጋጀት፣ ማጸደቅና በሥራ ላይ ማዋል
ሐ. የክፍሉን አባላት የሥራ ዝርዝር አዘጋጅቶ በአባላቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ማድረግ
መ. በሰ/ት/ቤቱ ይዞታ ሥር ያሉ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ የሚከናወኑ
የግንባታ “ጥገና” እድሳትና ማስዋብ ሥራዎችን መሥራትና መቆጣጠር
ሠ. ለሰ/ት/ቤቱ ኢኮኖሚያዊ አቅም በሚፈጥሩ የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ተግባራት ላይ
መሠማራት
ረ. በልማት ሥራዎች ዙሪያ ሥልጠና መስጠት፤
ሰ. የልማት ሥራዎችን የሽያጭና የአገልግሎት ዋጋን መወሰን’ገቢዎችን መሰብሰብና ለሰ/ት/ቤቱ
ሂሳብና ንብረት አስተዳደር ክፍል ገቢ ማድረግ
ሸ. የክፍሉን የፋይናንስ አስተዳደር ተቀባይነት ባላቸው የሂሳብ አያያዝ ሥርዓቶች መሠረት ማከናወን
ቀ. የክፍሉን የሥራ አፈጻጸምና የሂሳብ ሪፖርትን ለሥራ አመራሩ ማቅረብ፡፡
በ. በክፍሉ ይዞታ ሥር የሚገኙ ንብረትና ሰነዶችን በአግባቡ መያዝ፤
ተ. ከሌሎች የሰ/ት/ቤቱ የአገልግሎት ክፍሎች ጋር በጥምረት በመሥራት ለሰ/ት/ቤቱ ዓላማ መሳካት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ