ጨው አልጫ ቢሆን

ስራውን ዘንግቶ ቢከበው ስንፍና ከጥቅም የማይውል ሆኖ ቢቀር መና እንደባህሪው መጣፈጥ ቢያቅተው የኔ አይደለም ብሎ ድርሻውን ቢተወው ዘሩን አምሳያውን ከድንጋይ ተቆጥሮ መረገጡ አይቀርም መድቀቁ ተሰብሮ ይብላኝለት ለእርሱ ድርሻውን ላልሰራ ከድንጋዮች ተርታ ስሙ ለተጠራ (ወርቅነሽ ቱፋ)