የቤተክርስቲያንንና የሰ/ት/ቤቱን የመረጃ ሀብቶች እያሰባሰበ፣ እያደራጀና እየተንከባከበ የመጠበቅ፣ ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለማገናዘቢያ አገልግሎት ማቅረብ
ሀ. የክፍሉን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፣አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
ለ. የቤ/ክን እና የሰ/ት/ቤቱን አጠቃላይ መረጃ በተጠናከረና በተሟላ ሁኔታ ይሰበስባል፣ ይለያል፣ ያደራጃል፣ ይተነትናል፣ ደኅንነታቸውን ይጠብቃል፣ ለተጠቃሚዎች ያደርሳል፡፡
ሐ. ለቤ/ክን እና ለሰ/ት/ቤቱ ግብአት የሚሆኑ ማናቸውንም መረጃዎች ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመቀናጀት ያሰባስባል ለተፈላጊው ዓላማ ያውላል፡፡
መ. ከባለድርሻና ከተባባሪ አካላት ጋር ወቅታዊ መረጃዎችን ይለዋወጣል፡፡
ሠ. በቤ/ክ ላይ ያነጣጠሩ የአጽራረ ቤ/ክንን እንቅስቃሴዎች ይከታተላል፤ ተጨባጭ የሆነና በማስረጃ የተደገፈ መረጃ ሲያገኝ ለሚመለከታቸው አካላት ያስታውቃል ሂደቱንና ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፡፡
ረ. ከባለድርሻና ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ማዕከላዊ የመረጃ ቋት እና የቤተ-መጻሕፍት ማዕከል እንዲቋቋም ያደርጋል፡፡
ሰ. የመረጃ ፍሰቱን እና ደኅንነቱን ወጥ፣ ዘመናዊ እና አስተማማኝ ለማድረግ የሚያግዝ ቴክኖሎጂ እንዲዘረጋ ያደርጋል፡፡
ሸ. አግባብነት ያላቸው ማናቸውም መረጃዎች በተደራጀ ሁኔታ ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
ቀ. አጠቃላይ የቤ/ክን እና የሰ/ት/ቤቱን የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን ይሰራል፡፡
በ. የሰ/ት/ቤቱን ድህረ-ገጽ ያዘጋጃል፣ያስተዳድራል፡፡
ተ. ለሰ/ት/ቤቱ የአገልግሎት ክፍሎች ስለ-መረጃና መዛግብት ስራዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ያመቻቻል
ቸ. ከአገልግሎት ክፍላት ጋር በትብብር ይሰራል፡፡
ኀ. የሥራና አፈጻጸም ሪፖርት ለሥራ አመራሩ ያቀርባል፡፡
ነ. በስሩ ያሉ ንብረቶችን ይጠብቃል፣ደህንነታቸውን ይከታተላል፡፡