የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ትምህርቷ ማለትም ዶግማዊ፣ቀኖናዊ እና ትውፊቷን በሥነጥበባዊ መንገድ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት እና ምዕመናን ማድረስ ነው፡፡
ሀ. የክፍሉን መሪ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ለሰንበት ትምሕርት ቤቱ የሥራ አመራር ያጸድቃል፣
ይተገብራል ተፈጻሚነቱን ሪፖርት ያደርጋል፡፡
ለ. የሥነ ጽሑፍና የሥነ-ሥዕል እና ሌሎች የሥነ ጥበብ ተሰጥዖ እና ፍላጎት ያላቸውን አባላት
በመለየት በተለያዩ መርሐ ግብራት ላይ እንዲያቀርቡ ሁኔታዎች ያመቻቻል፡፡
ሐ. የተለያዪ የሥነ ጥበባዊ መርሐ ግብሮችን ያዘጋጃል፡፡
መ. ለአባላት ሥነ ጥበባዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ከ ትምሕርትና ስልጠና ክፍል ጋር በመሆን
ሥልጠና ይሰጣል፡፡