Astedadari

ደብራችንን የሚያስተዳድሩ አዲስ አስተዳዳሪ እና ዋና ጸሐፊ ምደባ ተደረገ

ደብራችንን የሚያስተዳድሩ አዲስ አስተዳዳሪ እና ዋና ጸሐፊ ምደባ ተደረገ

የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንን አስተዳዳሪ የነበሩት መላአከ ገነት መዝገቡ ላቀው አዲሱ የደብራችን አስተዳዳሪ ሁነው  ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በተጻፈ ደብዳቤ  የተመደቡ ሲሆን  በዛሬው ዕለት የአቀባበል መርሐ ግብር  የገዳማትና  አድባራት አስተዳዳሪዎች፣  የክፍለ ከተማው አመራሮች ፣ የደብሩ ማህበረ ካህናት እና ሰንበት ት/ቤት አባላት እንዲሁም  የአካባቢው አጥቢያ ምዕመናን በተገኙበት በደመቀ መልኩ  ተደርጎላቸዋል ፡፡
       
 ለክቡር አባታችን መልአከ ገነት መዝገቡ ላቀው  መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላችሁ አንቀጸ ብጹአን ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከልብ ይመኛል።

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *