ህጻናት ወደ ሰንበት ት/ቤት መጥተው እንዲማሩ ፣ በመንፈሣዊ እውቀታቸውናሕ ይወታቸው እንዲሁም በአስኳላ ትምህርታቸው እንዲበለጽጉ በማድረግ ውጤታማ የሆኑ የቤተክርስቲያንና የሀገር ተረካቢ ህጻናትን ማፍራት፡፡
ሀ. የክፍሉን ተግባራት ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል ሪፖርት ያደርጋል፣ ንብረትና
በጀት ይቆጣጠራል ያስተዳድራል፣ ግብአት ያሟላል፣ ብሎም ከክፍላት ጋር በትስስር
ይሰራል
ለ. ህጻናትን እንደ እድሜ አከፋፈላቸው መንፈሳዊ ት/ት ያስተምራል በቀለም ትምህርታቸው
እንዲበረቱ እገዛ ያደርጋል እንዲሁም ለህጻናጽና አገልጋዮች መንፈሳዊ ህይወታቸውን
የሚያጠናክሩበትን ውይይቶች ክህሎታቸውን የሚያሳድጉበትን ስልጠናዎችን ያመቻቻል
ሐ. ህጻናትን ያሬዳዊ መዝሙሮችን አውቀውና ጠንቅቀው እንዲያውቁ ብሎም በጸሎት
ህይወታቸው እንዲበረቱ ያደርጋል
መ. ህጻናት የስነ-ጥበብ እና የህይወት ክህሎት ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የተለያዩ
መርሃግብሮችን ይቀርጻል፤ይፈጽማል ብሎም ትምህርት አሰጣጡን ለህጻናት ምቹ
ለማድረግ ለህጻናት የሚሆኑ ጨዋታዎችን /ይሰበስባል/ ያዘጋጃል፣ ያስጠናል
ሠ. ህጻናትን ይጠራል፣ ይሰበስባል፣ ይመዘግባል፣ይይዛል፣ይከታተላል፣እድሜያቸው ሲደርስ
ወደ ወጣት እንዲሸጋገሩ ያመቻቻል፣በመንፈሳዊ ህይወትና በስነምግባር የታነጹ እንዲሆኑ
ከወላጆች /አሳዳጊዎች/ ጋር በጋራ ይሰራል
ረ. አገልጋዮችን ይመድባል፣ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣የጋራ መርሀ-ግብሮችን ያዘጋጃልብሎም
ህጻናት በክፍላት ውስጥና በመስክ አገልግሎቶች ላይ እንዲሳተፉ ይሰራል
ሰ. ህጻናትና አገልጋዮችየበጎ አድራጎትና እና የልማት ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ፣በማህበራዊ
ህይወት እንዲረዳዱና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ድጋፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል