ጨው አልጫ ቢሆን

ስራውን ዘንግቶ ቢከበው ስንፍና ከጥቅም የማይውል ሆኖ ቢቀር መና እንደባህሪው መጣፈጥ ቢያቅተው የኔ አይደለም ብሎ ድርሻውን ቢተወው ዘሩን አምሳያውን ከድንጋይ ተቆጥሮ መረገጡ አይቀርም መድቀቁ ተሰብሮ ይብላኝለት ለእርሱ ድርሻውን ላልሰራ ከድንጋዮች ተርታ ስሙ ለተጠራ (ወርቅነሽ ቱፋ)

311487397_638258941005462_6462202714429056284_n

ሁለቴ ተዳሰስ

አንድ አይበቃህም ተመለስ ራስህን ማወቅ ተስኖሃል ዛፉን ከሰዎች መለየት  እንዴት ይቻልሃል? የእውቀት ዓይንህ ሲበራ መዳሰስ ልመድ አንዳንዴ ተቀመጥ ከአባቶችህ እግር ብቃት አይገኝም በአንዴ ድጋሜ ተዳሰስ መጥተህ አይኖችህ አጥርተው ይዩ ተለማኝ ከለማኝ ዛፉን ከሰው እንዲለዩ (ወርቅነሽ ቱፋ)

163698700_443330390063797_3458997047476362961_n

የእኔ ነገር

ጴጥሮስን አማለው ጌታን ካደ ብዬ ከኃጢአት እሳት ዳር ከዓለም ጋር ቁጭ ብዬ ይሁዳ ነህ አልኩት አቅልዬ ወንድሜን ስንት ጊዜ ሽጬው ለውጬው ጌታዬን ሰጡት ብዬ አዝናለው ሰፍነግና ሃሞት ስግተው እየኖርኩ የኃጢአቴን ገፈት የዘመኑ ዴማስ እያልኩ እተቻለው ከነዓን ሳልገባ መንገድ ላይ እያለው እንዲህ ነኝ ስጠቁም ጣቴን ወደሌላ ለራሴ አበጅቼ የኃጢአት ከለላ & ...