በሰንበት ትምህርትቤታችን ሥር የሚገኙት ግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች መካከል ቁጥራቸው ከመቶ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ምርቃት በትናንትናው ዕለት ሰኔ 17 2015 ዓም በሰንበት ትምህርት ቤታችን አዳራሽ የቤተ አብርሃም ክፍል ተወካይ እና አስተባባሪዎቻቸው እንዲሁም የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ተከናውኗል።
ደብራችንን የሚያስተዳድሩ አዲስ አስተዳዳሪ እና ዋና ጸሐፊ ምደባ ተደረገ
ደብራችንን የሚያስተዳድሩ አዲስ አስተዳዳሪ እና ዋና ጸሐፊ ምደባ ተደረገ የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንን አስተዳዳሪ የነበሩት መላአከ ገነት መዝገቡ ላቀው አዲሱ የደብራችን አስተዳዳሪ ሁነው ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በተጻፈ ደብዳቤ የተመደቡ ሲሆን በዛሬው ዕለት የአቀባበል መርሐ ግብር የገዳማትና አድባ ...
የብጹዕ አቡነ መልኬጼዲቅ 13ኛ ዓመት መታሰቢያ
በአንቀጸ ብጹአን ሰንበት ተማሪዎች እና የአጥቢያው ወጣቶች ላይ ትልቅ አሻራ ያሳረፉት እና በርካታ ስራዎችን በህይወት ዘመናቸው ሰርተው ያለፉት አባታችን ብጹዕ አቡነ መልከጼዲቅ የከምባታ እና ሀዲያ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አባት ያረፉበትን 13ኛ ዓመት የእረፍታቸው መታሰቢያ ቀደምት የአባታችን ፍሬዎች ፣ መደበኛ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ...



