ጴጥሮስን አማለው ጌታን ካደ ብዬ
ከኃጢአት እሳት ዳር ከዓለም ጋር ቁጭ ብዬ
ይሁዳ ነህ አልኩት አቅልዬ ወንድሜን
ስንት ጊዜ ሽጬው ለውጬው ጌታዬን
ሰጡት ብዬ አዝናለው ሰፍነግና ሃሞት
ስግተው እየኖርኩ የኃጢአቴን ገፈት
የዘመኑ ዴማስ እያልኩ እተቻለው
ከነዓን ሳልገባ መንገድ ላይ እያለው
እንዲህ ነኝ ስጠቁም ጣቴን ወደሌላ
ለራሴ አበጅቼ የኃጢአት ከለላ
(ወርቅነሽ ቱፋ)
ጴጥሮስን አማለው ጌታን ካደ ብዬ
ከኃጢአት እሳት ዳር ከዓለም ጋር ቁጭ ብዬ
ይሁዳ ነህ አልኩት አቅልዬ ወንድሜን
ስንት ጊዜ ሽጬው ለውጬው ጌታዬን
ሰጡት ብዬ አዝናለው ሰፍነግና ሃሞት
ስግተው እየኖርኩ የኃጢአቴን ገፈት
የዘመኑ ዴማስ እያልኩ እተቻለው
ከነዓን ሳልገባ መንገድ ላይ እያለው
እንዲህ ነኝ ስጠቁም ጣቴን ወደሌላ
ለራሴ አበጅቼ የኃጢአት ከለላ
(ወርቅነሽ ቱፋ)