አንድ አይበቃህም ተመለስ
ራስህን ማወቅ ተስኖሃል
ዛፉን ከሰዎች መለየት
እንዴት ይቻልሃል?
የእውቀት ዓይንህ ሲበራ
መዳሰስ ልመድ አንዳንዴ
ተቀመጥ ከአባቶችህ እግር
ብቃት አይገኝም በአንዴ
ድጋሜ ተዳሰስ መጥተህ
አይኖችህ አጥርተው ይዩ
ተለማኝ ከለማኝ
ዛፉን ከሰው እንዲለዩ
(ወርቅነሽ ቱፋ)
አንድ አይበቃህም ተመለስ
ራስህን ማወቅ ተስኖሃል
ዛፉን ከሰዎች መለየት
እንዴት ይቻልሃል?
የእውቀት ዓይንህ ሲበራ
መዳሰስ ልመድ አንዳንዴ
ተቀመጥ ከአባቶችህ እግር
ብቃት አይገኝም በአንዴ
ድጋሜ ተዳሰስ መጥተህ
አይኖችህ አጥርተው ይዩ
ተለማኝ ከለማኝ
ዛፉን ከሰው እንዲለዩ
(ወርቅነሽ ቱፋ)