ደብራችንን የሚያስተዳድሩ አዲስ አስተዳዳሪ እና ዋና ጸሐፊ ምደባ ተደረገ
የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንን አስተዳዳሪ የነበሩት መላአከ ገነት መዝገቡ ላቀው አዲሱ የደብራችን አስተዳዳሪ ሁነው ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በተጻፈ ደብዳቤ የተመደቡ ሲሆን በዛሬው ዕለት የአቀባበል መርሐ ግብር የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የክፍለ ከተማው አመራሮች ፣ የደብሩ ማህበረ ካህናት እና ሰንበት ት/ቤት አባላት እንዲሁም የአካባቢው አጥቢያ ምዕመናን በተገኙበት በደመቀ መልኩ ተደርጎላቸዋል ፡፡
ለክቡር አባታችን መልአከ ገነት መዝገቡ ላቀው መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላችሁ አንቀጸ ብጹአን ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከልብ ይመኛል።

