
የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁአን ሰንበት ትምህርት ቤት በየአመቱ የሚያደርገውን የእለተ መፃጉዕ ጉዞ ሳርቤት አካባቢ ወደሚገኘው የጦር ጉዳተኞች ማዕከል በማድረግ መርሀግብሩን አከናውኗል።በእለቱም የማህበረ ቅዱሳን የወጣቶች በገና ዘማርያን ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን እለቱን የተመለከተው የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት በመምህር ዘላለም ታዬ ቀርቧል።ዘማሪት ሲስተር ሜላት ሰርገወርቅ እና ዘማሪ ዲ/ን ፍቅረሥላሴ ሙሉ በዝማሬ አገልግለውናል።የሰንበት ትቤታችን ዘማርያንም የእለቱን ያሬዳዊ ሀሌታ በዝማሬ በማቅረብ ተሳትፈዋል።በመጨረሻም ለተቋሙ የወንበር እና የአገልግሎት ነጠላ ከአባላት የተበረከተ ሲሆን የማዕከሉ ተወካዮችም በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ታላቅ ደስታ በቃልና ስለተቋሙ በሪፖርት መልክ በማቅረብ የእለቱ መርሀግብር ተጠናቋል።

