
የ2017ዓ/ም ዐቢይ ጾምን ምክንያት በማድረግ ስምንቱንም ሳምንታት ”ለመንገድ ስንቅ በእጃችሁ ያዙ” በሚል ርእስ ለአባላትና ለምዕመናን የተዘጋጀ ልዩ ጉባኤ ፫ ኛው ሰንበት ሙኩራብ በልዩ ልዩ መርሀግብራት ተከብሯል።የሰንበት ት/ቤታችን መዘምራን የዕለቱን ሀሌታ ቀለም በዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን፣የበገና ዝማሬ በመምህር አቤል ተስፋዬ ቀርቧል።በዕለቱም ልዩ ምክረ አበው መርሀግብር በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ እና በላዕከወንጌል ቀሲስ ጥላሁን ደሲሳ የበዓል መልእክት በሰፊው ተሰጥቷል።እንዲሁም የዕለቱ ዘማሪ ዘላለም ታከለ ዘጎላ በዝማሬ ያገለገለን ሲሆን የዕለቱ ጉባኤ አዘጋጅ የሰንበት ት/ቤቱ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ አጭር ሪፖርት በማቅረብ የመርሀግብሩ ፍፃሜ ሆኗል

