ጨው አልጫ ቢሆን

ስራውን ዘንግቶ ቢከበው ስንፍና

ከጥቅም የማይውል ሆኖ ቢቀር መና

እንደባህሪው መጣፈጥ ቢያቅተው

የኔ አይደለም ብሎ ድርሻውን ቢተወው

ዘሩን አምሳያውን ከድንጋይ ተቆጥሮ

መረገጡ አይቀርም መድቀቁ ተሰብሮ

ይብላኝለት ለእርሱ ድርሻውን ላልሰራ

ከድንጋዮች ተርታ ስሙ ለተጠራ

(ወርቅነሽ ቱፋ)

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *