የክፍሉ ዓላማ ዘመናዊና ውጤታማ የሒሳብና ንብረት አስተዳደር ሥርዓትን በሰንበት ትምሕርት ቤቱ ውስጥ በመዘርጋት የሒሳብና ንብረት አስተዳደር ሥራው በአግባቡ እንዲከናወን ማድረግ ነው፡፡
ሀ. የክፍሉን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ለሰንበት ትምሕርት ቤቱ የሥራ አመራር ያጸድቃል፣ይተገብራል
ተፈጻሚነቱን ሪፖርት ያደርጋል፡፡
ለ. የሰንበት ትምሕርት ቤቱን የሒሳብና ንብረት መረጃዎችን በዘመናዊ መንገድ ይይዛል
በተጠየቀም ጊዜ ያቀርባል፡፡
ሐ. የሰንበት ትምሕርት ቤቱን ማናቸውንም ገቢዎች ይሰበስባል ወደ ባንክም ገቢ ያደርጋል፡፡
መ. የክፍሉን የሥራ አፈጻጸምና የሰንበት ትምሕርት ቤቱን ሒሳብና ንብረት አስተዳደር ጉዳዮች
በተመለከተ ለሥራ አመራሩ ሪፖርት ያደርጋል፡፡
ሠ. በየክፍለ ቆጠራው የገንዘብና ንብረት ቆጠራ ያካሒዳል ወይም ቆጠራ እንዲካሔድና ሪፖርት
እንዲቀርብለት ያደርጋል፡፡
ረ. ለአባላቱ በሒሳብና ንብረት አስተዳደር ዙርያ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ ሁኔታዎችን
ያመቻቻል፡፡
ሰ. የክፍሉን የሥራ አፈጻጸምና የሰንበት ትምሕርት ቤቱን ሒሳብና ንብረትና አስተዳደር
ጉዳዮች በተመለከተ ሪፖርት ለሥራ አመራሩ ያቀርባል፡፡
ሸ. ሌሎች ክፍሉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል፡፡