Gabriel-Annunciation-to-Virgin-MARY-Vintage-Greek-_57

በዓለ ፅንሰት

በዓለ ፅንሰት

ዛሬ መጋቢት ፳፱ ዓለም የተፈጠረበት፣ ጌታ የተፀነሰበት፣ ሞትን ድል አድርጎ የተነሣበት፣ ይህ ዓለም የሚያልፍበት

ዛሬ ያ ነቢዩ ዳንኤልን ደም ግባቱ እስኪሽ ያስሰገደው መልአክ እየሰገደ በታላቅ ትሕትና የመጣበት ነው።

ካህኑ ዘካርያስን ከግርማው የተነሣ ያስደነገጠው መልአክ እየፈራ እየተባ እመቤታችንን ያበሠረበት ነው። ደነገጠች የሚል ቃል የተጻፈው መደነቋን ለማጠየቅ እንደኾነ ልብ እንበል።

ምክንያቱም የመልአኩ ሰላምታ አባታችን አዳም ከገነት ከተሰደደ ወዲህ ለማንም ያልተደረገ ነውና ከሰላምታው የተነሣ እንደኾነ ተጽፏልና።

ይልቁንስ መልአኩ ወደ እርሷ ገብቶ ማለቱን እናድንቅ። በልማድ ወዳለችበት ቤት ገብቶ ማለት ነው። ይህ ግን ከዚህም ይረቅቃል። ቅዱስ ዳዊት እና ነቢይ ሕዝቅኤል ቤተ መቅደስ ብለዋታልና ወደ እርሷ ገብቶ አለ።

ቅዱስ ገብርኤል እንደዚች ዕለት ጭንቅ ጥብብ ብሎት አያውቁም። ሳጥናኤል ሲያምጽ ጸንቶ አጸና እንጅ አልተብረከረከም። ወደ ድንግል ሲመጣ ግን ያ ሁሉ ግርማው ሳይለየው የሚበልጥ ግርማ ባላት ፊት ትሑት ኾነ።

ለእግዚአብሔር የሚሳነው የለም ብሎ የምታምነውን ሲነግራት ይኹንልኝ ይደረግልኝ አለችው እንጅ ብርቱ ፈተና ነበር የገጠመው።

ይኹንልኝ ባለችበት ቅጽበት ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ። ወልደ እግዚአብሔር እንዲህ ባለ ጥበብ እንጅ በኃይሉ ብቻ ሰው አልኾነም።

ሦስቱ ትሕትና

፩. የአምላክ ሰው መኾን ከአዕምሮ የሚያልፍ ትሕትና

፪. የእመቤታችን ትሕትና – እነሆኝ የጌታ ባሪያ

፫. የመልአኩ ትሕትና – እየሰገደ እያመሰገነ ገራም የኾነበት

ዲ/ን አባይነህ ካሴ

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *