የዐቢይ ጾም አራተኛ ሣምንት በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ...
ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት የተመሠረተው ጥቅምት 4 ቀን 1959 ዓ.ም ሲሆን በጊዜውም የነበረው ስያሜ የብሥራተ ገብርኤል ወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር የሚል ነበር፡፡ የመጀመሪያ ዓላማው “ሰው በእህል ብቻ አይኖርም በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ” ማቴ 4 ፥ 4 ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ እንደተነገረው ቃለ እግዚአብሔር ምግበ ነፍስ ምግበ ሥጋ እንደመሆኑ መጠን በዕለተ ሰንበት የሰንበት ትምህርት ከሚያስፈልጋቸው ተገልጋዮች መካከል አንዱ የሆኑት ወጣቶችና ሕፃናትን ለማስተማር ነበር፡፡ማኅበሩም እስከ 1968 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ በመሆን ሕልውናውን ለማቆየት ታግሏል፡፡ ከነዚህም መካከል በወቅቱ ሀገሪቱን ይመራ የነበረው ሥርዓት የእምነት ተቋማት ውስጥ የነበሩ ወጣቶች ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመግባት የራሳቸውን አስተምህሮ ለማራመድ መሞከራቸው ነበር፡፡

ቅዱሳን አባቶች ጠብቀው ያስረከቡንን የቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት አክብሮና አስከብሮ ተስፋ የምናደርገውን መንግሥተ ሰማያት ለመውረስ የሚያበቃ የጸና ሃይማኖትና ምሳሌ የሆነ ምግባር ይዞ የሚገኝ ጥበበኛ ትውልድን የሚያፈራ ሰንበት ትምህርት ቤት ተፈጥሮ ማየት።


ለመንግሥተ ሰማያት የሚያበቃ ሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት መማርና ማስተማር፤ የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖና ጠብቆ ማስጠበቅ ቤተክርስቲያን ለሀገርና ለማኅበረሰቡ መንፈሳዊና ሰብዓዊ ብልጽግና ልትወጣ የሚገባትን አስተዋጽኦ ማበርከት የሰንበት ትምህርት ቤቱን አባላት በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩቶ በማሳደግ የነገይቱ ቤተክርስቲያን ተረካቢ መሆን በሚያስችላቸው ደረጃ ማብቃት፡፡
በየሳምንቱ እሑድ በሰንበት ትምህርት ቤታችን በሚካሄደው ተከታታይ የወጣቶች ትምህርት ላይ በመገኘት ነፍስዎን ይመግቡ። ቃለ እግዚአብሔር፣ ያሬዳዊ ዝማሬ፣ ጸሎት መርሐ ግብራት ተዘጋጅተዋል
ሰንበት ትምህርት ቤታችን ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው ያዘዘንን በጎ ምግባራት በተቋም ደረጃ ይሠራል። ሕሙማንን መጠየቅ፣ ችግረኞችን በአልባሳት፣ በምግብ መርዳት እንዲሁም ራሳቸውን በሥራ እንዲችሉ እገዛ ያደርጋል።
ልጆች የሀገር እንዲሁም የቤተክርስቲያን የነገ ተረካቢዎች ናቸው። ሰንበት ትምህርት ቤታችንም ልጆች በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ታንጸው እንዲያድጉ ተከታታይ ትምህርቶችን በማስተማር ለሁለንተናዊ እድገታቸው ተጨንቆ ይሠራል፡፡
ብዙውን ጊዜ ወጣት ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ከብዙዎች ስሜት መረዳት እንደሚቻለው በኃጢአት ስንወድቅና በኛ ውስጥ ያለው ክርስቲያናዊ ማንነት ከሰዎች ሁሉ በተለየ መልኩ ቆሻሻ ሆኖና መስሎ ከታየን፤ ከቅድስት ቤተክርቲያን፤ ከጸጋው ግምጃ ቤት፤ ከምሕረቱ አደ ...
ትሕትና ምንድር ነው? ብዙ ጊዜ በእኛ ዘንድ የተናቀ ልብስ መልበስ ፣ አንገት መስበር ፣ ዝግ ብሎ ማውራት እና ‹እኔ በደለኛ የማይገባ ሰው ነኝ› እያሉ ደጋግሞ መናገር እንደ ትሑት ያስቆጥር ይሆናል፡፡ ነገር ግን የትሕትና ትርጉም ከዚህም በላይ ነው፡፡ ...