በደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብጹአን ሰንበት ት/ቤት

 

ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት የተመሠረተው ጥቅምት 4 ቀን 1959 ዓ.ም ሲሆን በጊዜውም የነበረው ስያሜ የብሥራተ ገብርኤል ወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር የሚል ነበር፡፡ የመጀመሪያ ዓላማው “ሰው በእህል ብቻ አይኖርም በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ” ማቴ 4 ፥ 4 ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ እንደተነገረው ቃለ እግዚአብሔር ምግበ ነፍስ ምግበ ሥጋ እንደመሆኑ መጠን በዕለተ ሰንበት የሰንበት ትምህርት ከሚያስፈልጋቸው ተገልጋዮች መካከል አንዱ የሆኑት ወጣቶችና ሕፃናትን ለማስተማር ነበር፡፡ማኅበሩም እስከ 1968 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ በመሆን ሕልውናውን ለማቆየት ታግሏል፡፡ ከነዚህም መካከል በወቅቱ ሀገሪቱን ይመራ የነበረው ሥርዓት የእምነት ተቋማት ውስጥ የነበሩ ወጣቶች ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመግባት የራሳቸውን አስተምህሮ ለማራመድ መሞከራቸው ነበር፡፡ 

Read more 

ርዕይ

ቅዱሳን አባቶች ጠብቀው ያስረከቡንን የቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት አክብሮና አስከብሮ ተስፋ የምናደርገውን መንግሥተ ሰማያት ለመውረስ የሚያበቃ የጸና ሃይማኖትና ምሳሌ የሆነ ምግባር ይዞ የሚገኝ ጥበበኛ ትውልድን የሚያፈራ ሰንበት ትምህርት ቤት ተፈጥሮ ማየት።

እሴት

ዓላማ

ለመንግሥተ ሰማያት የሚያበቃ ሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት መማርና ማስተማር፤ የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖና ጠብቆ ማስጠበቅ ቤተክርስቲያን ለሀገርና ለማኅበረሰቡ መንፈሳዊና ሰብዓዊ ብልጽግና ልትወጣ የሚገባትን አስተዋጽኦ ማበርከት የሰንበት ትምህርት ቤቱን አባላት በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩቶ በማሳደግ የነገይቱ ቤተክርስቲያን ተረካቢ መሆን በሚያስችላቸው ደረጃ ማብቃት፡፡

በሰንበት ትምህርት ቤታችን ከሚሰጡ አገልግሎቶች በጥቂቱ

admin-ajax2

ተከታታይ ትምህርት

በየሳምንቱ እሑድ በሰንበት ትምህርት ቤታችን በሚካሄደው ተከታታይ የወጣቶች ትምህርት ላይ በመገኘት ነፍስዎን ይመግቡ። ቃለ እግዚአብሔር፣ ያሬዳዊ ዝማሬ፣ ጸሎት  መርሐ ግብራት ተዘጋጅተዋል

ለመሳተፍ ይህን ይጫኑ
admin-ajax 22

ግብረ አብርሃም

ሰንበት ትምህርት ቤታችን ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው ያዘዘንን በጎ ምግባራት በተቋም ደረጃ ይሠራል። ሕሙማንን መጠየቅ፣ ችግረኞችን በአልባሳት፣ በምግብ መርዳት እንዲሁም ራሳቸውን በሥራ እንዲችሉ እገዛ ያደርጋል።

ለመርዳት ይህንን ይጫኑ
admin-ajax 222

የልጆች አስተዳደግ

ልጆች የሀገር እንዲሁም የቤተክርስቲያን የነገ ተረካቢዎች ናቸው። ሰንበት ትምህርት ቤታችንም ልጆች በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ታንጸው እንዲያድጉ ተከታታይ ትምህርቶችን በማስተማር ለሁለንተናዊ እድገታቸው ተጨንቆ ይሠራል፡፡

ለማስመዝገብ ይህንን ይጫኑ

የቅርብ ጊዜ ትምህርቶች

ccb755523df7267a813c9531fd378f81

መጻጉዕ

የዐቢይ ጾም አራተኛ ሣምንት በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ...

Capture

ኃጢአተኛ ከሆንክ በቅድስናው ደጅ ምን ትሠራለህ?

ብዙውን ጊዜ ወጣት ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ከብዙዎች ስሜት መረዳት እንደሚቻለው በኃጢአት ስንወድቅና በኛ ውስጥ ያለው ክርስቲያናዊ ማንነት ከሰዎች ሁሉ በተለየ መልኩ ቆሻሻ ሆኖና መስሎ ከታየን፤ ከቅድስት ቤተክርቲያን፤ ከጸጋው ግምጃ ቤት፤ ከምሕረቱ አደ ...

photo_2023-05-16_12-25-23

ልደታ ለማርያም

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል አደረሰን!!! ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከተለዩ የተለየች፣ ከተመረጡ የተመረጠች ክብርት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በከበረች ቀን ግንቦት አንድ ቀን ተወለደች፡፡ የመወለዷም ...

gettyimages-667609663-612x612

ትሕትና ምንድር ነው?

ትሕትና ምንድር ነው? ብዙ ጊዜ በእኛ ዘንድ የተናቀ ልብስ መልበስ ፣ አንገት መስበር ፣ ዝግ ብሎ ማውራት እና ‹እኔ በደለኛ የማይገባ ሰው ነኝ› እያሉ ደጋግሞ መናገር እንደ ትሑት ያስቆጥር ይሆናል፡፡ ነገር ግን የትሕትና ትርጉም ከዚህም በላይ ነው፡፡ ...

Shopping Basket