ዐቢይ ዓላማ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምህርቷ ማለትም ዶግማዋ፤ቀኖናዋ ተውፊቷ ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለአጥቢያው ምዕመናን በተለይም ለሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ወቅቱ በሚፈቅደው ሁኔታ ቃለ እግዚአብሔር ማድረስና ትውልዱ በክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ታንጾ በሙያው ሀገሩንና ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግል ማድረግ ነው
ዝርዝር ዓላማ
– በሰንበት ትምህርት ቤታችን ውስጥ ያሉ አበላትን በተዘረጋው የስርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲያልፉ ማድረግ
– ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሰንበት ትምህርት ቤታችን መደበኛ ጉባኤ ላይ ቃለ እግዚአብሔር እንዲሰጥ ማድረግ
– መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ጉባኤያትን በመዘርጋት የአባላት ሕይወት በቃለ እግዚአብሔር እንዲታነጽ ማድረግ
– ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠት
– ካህናትና ዲያቆናትን ማፍራት
– ለሰሌዳ፤ለዩቱብ፤ለድህረገጽ፤ለጉባኤ፤ለበዓላት፤ የሚሆኑ ጹሁፎችን ማዘጋጀት
ሥርዓተ ትምህርትን ማስተግበር ፤መከታተል፤ እና ሥርዓተ ትምህርት ያልተዘጋጀላቸውን ጉዳዮች መነሻ የሚሆን ነገር ማዘጋጀት
– ለሰሌዳ፤ለዩቱብ፤ለድህረገጽ፤ለጉባኤ፤ለበዓላት፤ የሚሆኑ ጹሁፎችን ማዘጋጀት
– በብስራት መጽሔትና በበራሪ ወረቀቶች ትምህርት ማስተላለፍ
– በሰንበት ትምህርት ቤታችን ለተዘረጉ ጉባኤያት መምህርንን መመደብ
– ተተኪ መምህራንን ማፍራት
– ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላትና ለአካባቢው ምእመናን አብነት ትምህርት መስጠት
– በሰንበት ትምህርት ቤታችን የሚታዩ ችግሮችን ጥናት በማጥናት ስልጠናዎችን መስጠት
– ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላትና ለአካባቢው ምእመናን በተለያዩ በመንፈሳዊ፤በማህበራዊ፤በፍቅር ሕይወታቸው ምክክር ማድረግ
– በሰንበት ትምህርት ቤታችን ውስጥና ከሌሎች ደብራት ለሚመጡ መምህር መድቡልን ጥያቄ መምህር መመደብ