ወጫዊ እና ውስጣው መልካም ግንኙነቶችን በመፍጠር ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት ዐዲስ ክርስቲያኖችን መጥራት የገቡትንም መንፈሳዊ ሕይወታቸውን መከታተል ማጽናት የቅዱሳንንና የቅዱሳት መካናትን በረከት ማሣተፍ እና የስድስቱ ቃላተ ወንጌል ትዕዛዛትን ለመፈፀም ማስቻል፡፡
የሰ/ት/ቤቱ ቤተ አብርሀም ክፍል የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል
ሀ. የክፍሉን የሥራ እቅድና የበጀት ረቂቅን በማዘጋጀት ማጸደቅ፣ ተግባራዊ ማድረግ፤
ለ. የሰንበት ትምህርት ቤቱን መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ መርሐግብሮችን ማስተባበር፤
ሐ. በሰንበት ትምህርት ቤቱ ሥር ያሉትን ጊቢ ጉባኤያት ማስተባበር፤
መ. የተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርትን ያስተባብራል፣ ማስታወቂያ ይለጥፋል፣ ይመዘግባል፣ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽ/ቤትጋር በመተባበር ያስመርቃል፤
ሠ. አባላቱ ቅዱሳንን እንዲዘክሩ ያስተባብራል፤
ረ. በልማት ሥራዎች ዙሪያ ሥልጠና መስጠት፤
ሰ. የጉዞ መርሐ ግብር በማዘጋጀት ቅዱሳን መካናትን ያስጎበኛል ከበረከቱ ተካፋይ እንዲሆን ያደርጋል፤
ሸ. ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን አብያተ ክርሰቲያናት በመለየት ድጋፍ እንዲደረግላቸው ያስተባብራል፤
ቀ. ለስድስቱ ቃላተ ወንጌል ተግባራዊነት ይሠራል፤
በ. ውጫዊ እና ውስጣው የግንኙነት ሥራዎችን ይሠራል፤
ተ. የጠፉ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላትን በማፈላለግ ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቱ እንዲመለሱ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡